Dechasa Abebe

Dechasa Abebeዶ/ር ደቻሳ አበበ በጥቅምት 3፣ 1967 ዓ. ም በሰሜን ሸዋ ሳያደብርና ዋዩ ወረዳሳክላ አቦ የገጠር ቀበሌ ተወለደ። የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በደነባ አንደኛ ደረጃ፣ ሁለተኛ ደረጃውን በእነዋሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል። የመጀመሪያ ድግሪውን ከኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በታሪክ መምህርነት በ1991 ዓ. ም፣ የማስተርስ ድግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ በ1995 ዓ. ም እና ከኢንድራጋንዲ ዩኒቨርሲቲ በሶሽዮሎጂ በ2001 ዓ. ም ያገኘ ሲሆን በታሪክ የትምህርት ዓይነት ደግሞ የዶክትሬት ድግሪ በ2008 ዓ. ም ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ተቀብሏል። ዶ/ር ደቻሳ በጋምቤላ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ፣ በጅማ ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ መምህርነት ያገለገለ ሲሆን አሁን በዚያው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚገኘው የአፍሪካ ጥናትና ምርምር ማዕከል በመምህርነትና በተመራማሪነት በማገልገል ላይ ይገኛል። በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ በርካታ የጥናት ወረቀቶችን በተለያዩ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚገኙ የምርምር ጆርናሎች ላይ አሳትሟል። Read More Read Less

3 results found
List viewGrid view
Sort By:
No more records found